Fana: At a Speed of Life!

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር  17 የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤት  እድሳት አስጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በአዲስ አበባ አስተዳደር ጉለሌ ክፍለ ከተማ የተጎሳቆሉና ለኑሮ ምቹ ያልሆኑ 17 የአቅመ ደካሞችን የመኖሪያ ቤቶች እድሳት አስጀምሯል፡፡

ሚኒስትሯ  ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በዛሬው ዕለት የተጎሳቆሉ የመኖሪያ ቤቶችን ከሚኒስቴሩ የስራ ኃላፊዎች፣ ከተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች፣ ዕድሳቱን ለማከናወን ፈቃደኛ ከሆኑ ኮንትራክተሮችና ከክፍለ ከተማው አመራሮችና የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ጋር በጋራ በመሆን አስጀምረዋል፡፡

ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት÷ የአቅመ ደካሞቹን መኖሪያ ቤቶች ለማደስ ቃል የገቡ የስራ ተቋራጮችንና ተጠሪ ተቋማትን አመስግነዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአቅመ ደካሞችን ቤቶች አፍርሶ የመስራት ስራውን ወደ ፊትም በቀጣይነት አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ይህን መሰሉ የበጎ አድራጎት ተግባር አቅመ ደካማ ዜጎች   ̎ተመልካች ወገን አለኝ… ከጎንህ ነኝ የሚል መንግስትና ህዝብ አለኝ”  እንዲሉ የሚያደርግ፣የመረዳዳትና የመተሳሰብ ባህላችንንም የሚያጠናክር ነው ብለዋል።

ሚኒስትሯ አያይዘውም በኢትዮጵያ ተጠናክረው እየቀጠሉ ያሉት  የበጎ  ፈቃድ ስራዎችም ይበልጥ መዳበር ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ሚኒስቴር  መስሪያ ቤቱም የመኖሪያ ቤቶቹን እድሳት  በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቅቆ ለመኖሪያ ቤት ባለቤቶች እንደሚያስረክብም ቃል መግባታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.