Fana: At a Speed of Life!

በባህርዳር ከተማ በ34 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህርዳር ከተማ በ34 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ (ፉኮካ) ፕሮጀክት ተመረቀ።
በምረቃ ስነ ሥርዓቱ የከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድን ጨምሮ ሌሎች የፌደራል፣ የክልልና የከተማ አመራሮች እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ አጋር አካላት ተገኝተዋል።
ፕሮጀክቱ ከተማ አስተዳደሩ ከዩኤን ሀቢታት ድርጅት ጋር በመተባበር በጃፓን መንግስት ድጋፍ በ34 ሚሊየን ብር የተገነባ መሆኑን የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ ተናግረዋል።
ከንቲባው ፕሮጀክቱ በከተማዋ የሚታየውን የቆሻሻ አወጋገድ ችግር መፍታት እንደሚያስችል መግለጻቸውን ከባህርዳር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የዩኤን ሀቢታት ባህርዳር ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ብርሃኑ እስከዚያ÷ ባህርዳር ከተማን የሚመጥን የቆሻሻ መስወገጃ ዘዴ አለመኖሩን ተከትሎ በጃፓን ዩኒቨርሲቲ ሜቴን የተባለ ኬሚካል ተዘጋጅቶና በ34 ሚሊየን ብር ድጋፍ ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል።
ይህም በከተመዋ የሚመረተውን ደረቅም ይሁን ፈሳሻ ቆሻሻ በፎኮካ ዘዴ በክለትን ከመቀነስ ባለፈ የከርሰ ምድር ውሃ ብክለት እና የግሪን ሀውስ ልቀት እንዳይፈጠር በማድረግ 100 ሺህ ኪዩቢክ ሜትር ቆሻሻ ማስወገድ እንደሚያስችል ገልፀዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person, standing and outdoors
39
2 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.