Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል የጸጥታ ሃይል ከመከላከል ወደ ማጥቃት እንዲሸጋገር መመሪያ ተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል በህወሃት የሽብር ቡድን በሶስት ግንባር በተከፈተበት ይፋዊ ጦርነት ራሱን ከመከላከል ወጥቶ ወደ ማጥቃት ለመሸጋገር ወሰነ፡፡
የአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የአማራ ክልል በህወሃት አሸባሪ ቡድን በዋግ ግንባር አበር ገሌ እና ፀጋብቲ፣ በራያ ግንባር በኮረም፣ አላማጣ እና ባላ፣ በወልቃይት ግንባር በማይፀብሪ እና በጠገዴ ለተከፈተበት ይፋዊ ጦርነት ራሱን ከመከላከል ወጥቶ ወደ ማጥቃት እንደዲሸጋገር መወሰኑን አስታውቀዋል።
ክልሉ በሦስቱ ግንባሮች የተከፈተበት ጦርነት ዓለም አቀፋዊ የጦርነት ህጎችን በሚፃረር መልኩ ህፃናት፣ አረጋውያንን፣ የኃይማኖት አባቶች እና ሴቶችን ከፊት በማሰለፍ ንፁኃንን በመተንኮስ እና በመግደል የታጀበ ይፋዊ ጦርነት እንደሆነ መግለጻቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
እስካሁን ድረስ ክልሉ ወራሪውን ኃይል ለመከላከል እና ለመመከት ብቻ ሲጥር እንደቆየ በመግለፅ፣ ከዚህ በኋላ ግን የክልሉ ልዩ ኃይል እና አጠቃላይ የፀጥታ አካላት ወደ ማጥቃት እንዲሸጋገሩ ትእዛዝ መሰጠቱን ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለፁት።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.