Fana: At a Speed of Life!

ዚምባብዌ ከሙስና ጋር ተያይዞ የዑጋንዳን ድጋፍ መጠየቋ የሀገሪቱን ዜጎች አስቆጥቷል

አዲስ አበባ፣ ጥር 18 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዚምባብዌ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሉክ ማላባ የዑጋንዳ ዳኞች የሀገራቸውን ዳኞች በፀረ ሙስና ዙሪያ ስልጠና እንዲሰጧቸው ግብዣ ማቅረባቸውን ተከትሎ ዚምባብዌያውያን ተቃውሞ እያሰሙ ነው።

ተቃውሞው “ዑጋንዳ በፀረ ሙስና ትግል ዙሪያ ልንማርባት የምትችል ሀገር አይደለችም” ከሚል የመነጨ መሆኑም ተገልጿል።

ይህንን ተከትሎም የሀገርን ሀብት ማባከን አቁሙ ሲሉም መንግስትን እየጠየቁ እደሚገኝም ነው የተነገረው።

ታኩድዝዋ ሙናንግዋ የተባለ ግለሰብ በማህበራዊ ትስስር ገፁ “ዑጋንዳ ሙስናን ለመታገል ጥሩ ምሳሌ አይደለችም” ሲል ገልጿል፤ ምናልባት ሩዋንዳ፣ ሲንጋፖር ፣ ኔዘርላንድስ፣ ማሌዢያ እና ሌሎችም በማለት አስፍሯል።

ሉካ ማላባ የዑጋንዳ ልዑክ በዚምባብዌ ዋና ከተማ ሀራሬ በፀረ ሙስና ዙሪያ ስልጠና እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

እርሳቸው ለዓመታት በጥፋተኞች ላይ እርምጃ ከወሰደችው ዑጋንዳ ዚምባብዌ በርካታ ነገሮችን ትማራለች ብለዋል።

ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ባወጣው የ2019 የሃገራት የሙስና ደረጃ ዑጋንዳ ከ180 ሀገራት በ137ኛ ስትቀመጥ ዚምባብዌ 158ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ሆኖም የዚምባብዌ ጎረቤት የሆኑት ቦትስዋና፣ ናሚቢያ እና ደቡብ አፍሪካ በትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የ2019 መረጃ ከዑጋንዳ በተሻለ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.