Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት የተኩስ አቁም ውሳኔውን ውድቅ በማድረግ ስደተኞች በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ሳይቀር አዳዲስ ጥቃቶች መክፈቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በመንግስት የተላለፈውን የተናጠል የሰብዓዊ የተኩስ አቁም ውሳኔ ውድቅ በማድረግ ስደተኞች በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ሳይቀር አዳዲስ ጥቃቶች መክፈቱን የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ባለከው መግለጫ እንደገለጸው፤ ህወሓት የመንግስትን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ውድቅ አድርጎ ስደተኞች ላይ ጥቃት እየፈጸመ ነው።

በዚህ የህወሓት ጥቃት ምክንያት በማይ-ዓይኒ እና በአዲ-ሐሩሽ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙት ኤርትራዊያን ስደተኞች ደህንነታቸው ላይ አደጋ ላይ እንደወደቀ ኤጀንሲው አስታውቋል።

በዚህም የተነሳ ደህንነታቸው ሊጠበቅ ወደሚችልባቸው አካባቢዎች እንዲዛወሩ፣ በድጋፍ ላይ የተመሠረተ የከተማ ስደተኝነት እውቅና እንዲሰጣቸው እና ወደ ሶስተኛ ሀገር እንዲዛወሩ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጥያቄ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ብሏል፡፡

በችግሩ ዙሪያ ከስደተኞች ተወካዮች ጋር ተከታታይ ውይይቶችን ካሄዱን የገለጸው ኤጀንሲው፤ በሐምሌ 6 ቀን 2013 ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽነር የኢትዮጵያ ተወካይ በተገኙበት በመመስረት ላይ በሚገኘው የስደተኞች መጠለያ በሚገኝበት ዓለም-ዋጭ በመገኘት ከስደተኛ ተወካዮች ጋር ውይይት ተደርጓል ብሏል፡፡

“መንግስት የስደተኞች ድምጽ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ይደመጣል በሚል ተስፋ በአዲስ መጠለያ ጣቢያ ለማስፈር እና በድጋፍ ላይ የተመሠረተ የከተማ ስደተኝነት እውቅና ለመስጠት ጠንክሮ እየሠራ ይገኛል ብሏል፡፡

በመንግሥት በኩል እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን እና ለውጦችን በመረዳት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ውጤታማ እና ተጨባጭ ድጋፎችን በማድረግ ስደተኞችን በአዲስ መጠለያ ጣቢያ የማስፈሩን ሂደት ለማፋጠን የሚደረገውን ጥረት እንዲያግዙ ጥሪ እናቀርባለን” ሲልም ኤጀንሲው በመግለጫው አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.