Fana: At a Speed of Life!

ኒውዮርክ ታይምስና አሶሼትድ ፕሬስ ህወሓት ህጻናትን ለውትድርና መጠቀሙን አሞካሽተው መዘገባቸው የሚያሳዝን ነው – ቢለኔ ስዩም

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኒውዮርክ ታይምስና አሶሼትድ ፕሬስ ህወሓት ህጻናትን ለውትድርና መጠቀሙን አሞካሽተው መዘገባቸው የሚያሳዝን መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪ ቢለኔ ስዩም ገለጹ።

ቢለኔ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ኒውዮርክ ታይምስ እና አሶሼትድ ፕሬስ በዘገባዎቻቸው ላይ ህወሓት ህጻናትን ለውትድርና መጠቀሙን አሞካሽተው ማቅረባቸው የሚያሳዝን ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አሶሸትድ ፕሬስ እና ኒውዮርክ ታይምስ በተደጋጋሚ አሸባሪው ህወሓትን የተመለከቱ ሚዛናዊ ያልሆኑ የአንድ ወገን ዘገባዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል።

በተለይም የሀገር መከላከያ ሰራዊት የመንግስትን የተናጥል የተኩስ አቁም ውሳኔ ተከትሎ ከክልሉ ከወጣ በኋላ በንጹሀን ዜጎች ላይ እንዲሁም በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ የሚፈጸሙ ግድያዎችንና ዝርፊያዎችን በዝምታ ማለፋቸውን የኢፕድ ዘገባ ያመላክታል።

ከሰሞኑም አሸባሪው ድርጅት የመንግስትን የተናጥል የተኩስ አቁም እርምጃ ወደ ጎን በማለት በአማራና በአፋር ክልል በኩል ጥቃት እየፈጸመ መሆኑን በማወደስ ህወሓት ግዛቱን አስመለሰ የሚል ዘገባዎች ሲሰሩ ተስተውለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.