የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያ ክልል መንግስት 6 ሺህ 111 የውሀ መሳቢያ ሞተሮችን ለአርሶ አደሮች አስረከበ

By Meseret Awoke

July 15, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኦሮሚያ ክልል መንግስት ለበጋ ወራት የመስኖ ልማት ስራ የሚውሉ 6 ሺህ 111 የውሀ መሳቢያ ሞተሮችን የክልሉ ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት በዛሬው እለት ለአርሶ አደሮች አስረክቧል።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በሞጆ ከተማ ተገኝተው ከተለያዩ ዞኖች ለተውጣጡ አርሶ አደር ተወካዮች ድጋፉን አበርክተዋል።

4 ሺህ 111 የውሃ መሳቢያ ሞተሮች በመንግስት ወጪ ለአርሶ አደሩ በብድር የሚተላለፍ ሲሆን፥ 2ሺህ ደግሞ በግብርና እድገት ፕሮግራም በስጦታ የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

የውሃ መሳቢያ ሞተሮቹ 2ሺህ 555 ሄክታር መሬት ማልማት የሚችሉ መሆኑም በርክክብ ስነ -ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

የክልሉ መንግስት በመጀመሪያ ዙር 3 ሺህ 670 በላይ የውሃ መሳቢያ ሞተሮችን ለአርሶ አደሮች ማበርከቱንም ኦቢኤን ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!