Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ከሌጅ አውሮፕላን ማረፊያ ጋር በጭነት አገልግሎት ያለውን ውል አራዘመ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቤልጂየሙ ሌጅ አውሮፕላን ማረፊያ ጋር በጭነት አገልግሎት ያለውን ውል ለተጨማሪ አመታት አራዘመ፡፡

አየር መንገዱ ከአውሮፕላን ማረፊያው ጋር ለቀጣዮቹ አምስት አመታት ነው ውሉን ያራዘመው፡፡

በዚህም የሌጅ አውሮፕላን ማረፊያ በአፍሪካ እና አውሮፓ መካከል የጭነትና የሎጂስቲክስ አገልግሎት መተላለፊያ ሆኖ እንደሚያገለግል የኤር ካርጎ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት 15 አመታት ከሌጅ አውሮፕላን ማረፊያ ጋር በመተባበር በአውሮፓ የተሳካ የጭነት አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.