ስፓርት

የሴካፋ ከ23ዓመት በታች ውድድር ቅዳሜ ይጀመራል

By Meseret Awoke

July 15, 2021

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) ከ23ዓመት በታች ውድድር ቅዳሜ እንደሚጀምር ተገለጸ።

ኢትዮጵያ የምታስተናግደው ይህ ውድድር ተጋባዧን ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክን ጨምሮ ዘጠኝ የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ሀገራት በባህርዳር ይሳተፋሉ።

ውድድሩም የፊታችን ቅዳሜ በ9 ሰዓት ኢትዮጵያ ከኤርትራ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል።

የውድድሩ መክፈቻ ከቀኑ 8ሰዓት መሆኑንም ከኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!