Fana: At a Speed of Life!

በጀርመን በጎርፍ አደጋ የ42 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀርመን በደረሰ የጎርፍ አደጋ የ42 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡

አደጋው በሃገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል የደረሰ ሲሆን፥ ከሟቾች በተጨማሪ በርካቶች የገቡበት አለመታወቁን ፖሊስ ገልጿል፡፡

አስከፊ የተባለው ይህ የጎርፍ አደጋ የደረሰው በሪንላንድ ፓላቲን እና በሰሜን ሪን ዌስት ፋሊያ አካባቢዎች እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በእነዚህ አካባቢዎች በደረሰው የጎርፍ አደጋ ትልልቅ ህንፃዎችና ተሽከርካሪዎች በጎርፍ መወሰዳቸው ነው የተነገረው፡፡

የጎርፍ አደጋው ከጀርመን በተጨማሪ በቤልጂየም፣ በኔዘርላንድስ እና በአንዳንድ የምዕራብ አውሮፓ ሃገራት ተከስቶ የህይወትና የንብረት ጉዳት ማድረሱን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.