የሀገር ውስጥ ዜና

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከምርምር ዩኒቨርሲቲዎች አሸናፊ ሆነ

By Tibebu Kebede

July 15, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ጎንደር እና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን በማስከተል ጅማ ዩኒቨርሲቲ አሸናፊ ሆኗል።

በአመራር ብቃታቸው ሀዋሳ እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አመራሮችን በማስከተል የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል አባፊጣ አንደኛ ወጥተዋል።

በላቀ የፈጠራ ውጤት አንደኛ የላቀ አፈፃፀም ሰርተፊኬት፣ ሜዳልያ እና 250 ሺህ ብር ተሸላሚ ጀርሚያባ ባይሳ እና ቦዔዝ ብርሃኑ ሆነዋል።

ዶክተር አዲሱ በፍቃዱ ሁለተኛ በመውጣት የላቀ አፈፃፀም ሰርተፊኬት፣ ሜዳልያ እና 200 ሺህ ብር ተሸልመዋል።

ደራርቱ ደረጀ እና ሽመልስ ንጉሴ ደግሞ በእኩል ነጥብ ሶስተኛ በመውጣት የላቀ አፈፃፀም ሰርተፊኬት፣ ሜዳልያ እና 150 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በመምህራን ዘርፍ ዶክተር ሙሉእመቤት አበራ እና ዶክተር ዮሐንስ የላቀ አፈፃፀም ሠርተፊኬት፣ ሜዳልያ እና 25 ሺህ ብር ተሸላሚዎች ሆነዋል።

ተማሪ ሳባ ደስታ እና መስቀሉ ዳንኤል በምስጉን ታታሪ ተማሪዎች ዘርፍ የላቀ አፈፃፀም ሰርተፊኬት፣ ሜዳልያ እና የ7 ሺህ ብር ተሸላሚ መሆናቸውን ከዩኒቨርስቲው ድረ ገፅ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!