ስፓርት

የኦሮሚያ ስፖርት ኮሚሽን ከ2ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ቁሳቁስ ለዞኖች ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

July 15, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ስፖርት ኮሚሽን ከ2ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ቁሳቁስ ለዞኖች ድጋፍ አድርጓል።

የርክክብ ስነ-ስርዓቱ አዲስ አበባ በሚገኘው የኦሮሚያ ስፖርት ኮሚሽን ቅጥር ግቢ የተካሄደ ሲሆን፤ በዚሁ መረት በከተማ አስተዳደር ለሚተዳደሩ 13 ከተሞች የሞተር ሳይክል ስጦታ፣ለዞኖችና በከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ ለሁሉም ከተሞች ደግሞ ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ ለስፖርት ቅስቀሳ መገልገያ የሚሆን ሞንታርቦ ተበርክቶላቸዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ዞኖችና በከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ ከተሞች የተደረገላቸው ድጋፍ ጠቃሚ መሆኑንና ነባራዊ የቢሮ መገልገያ ውስንነት ችግርን እንደሚቀርፍ ገልጸዋል።

በአጠቃላይ የሞተር ሳይክል ድጋፍ የተደረገላቸው ከተሞች ሞጆ፣ዱከም፣ቡራዩ፣ ሰበታ፣ ጅማ፣ወሊሶ፣ ሻሸመኔ፣ አሰላ፣ሮቤ፣ሱሉልታ፣ ቢሾፍቱና ጥቁር ውኃ መሆናቸውን ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!