የሀገር ውስጥ ዜና

አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን የማፈራረስ የጋራ ዓላማ ካላቸው ሃይሎች ጋር እየሰራ ነው – ዶክተር አለሙ ስሜ

By Meseret Awoke

July 15, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን የማፈራረስ የጋራ ዓላማ ካላቸው ሃይሎች ጋር እየሰራ ነው” ሲሉ በዴሞክራሲ ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜ ገለጹ።

የሰሙኑን የአሸባሪ ህወሓት ትንኮሳ ከኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ጋር የሚያያዝ መሆኑን አስተባባሪ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ አመላክተዋል።

በዚህም አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን በመራበት ዓመታት ሁሉ ኢትዮጵያን አንድ እንዳይሆኑ መስራቱን አስታውሰው፥ በኃይማኖት፣ በብሔርና በተለያየ አግባብ ሲከፋፍል መቆየቱን ሁሉም እንደሚያውቀው ገልጸዋል።

በተለይ ወጣቱ ባደረገው መራራ ትግልና በመንግስት ውስጥ ያሉ ለውጥ ፈላጊ ሀይሎች ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ትግል አሸባሪው የህወሃት ቡድን ማዕከላዊ የፖለቲካ ስልጣኑን ማጣቱን አስታውሰዋል።

ይህው የአሸባሪ ቡድን ከተጠያቂነት ለማምለጥ በመቀሌ ተሰባስቦ መቆየቱን ጠቅሰው፥ ”እኔ የማልመራት ኢትዮጵያ አትኖርም” በማለት የአገር መከላከያ ሠራዊቱን መውጋቱንም አውስተዋል።

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አሸባሪው የአገር መከላከያ ሠራዊትን በማጥቃት የአገር ሉዓላዊነትን በመዳፈር “አገርን የማፍረስ ሙከራ አድርጓል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!