Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተግዳሮቶችና ከህዝብ በሚነሱ ቅሬታዎች ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስአበባ ከተማ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተግዳሮቶችና ከህዝብ በሚነሱ ቅሬታዎች ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ነው።
በመድረኩ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ ሽፈራው ተሊላን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
በከተማዋ የተወሰኑ ክፍለ ከተሞች የሀይል ማነስና መቆራረጥ፥ የአገልግሎት ክፍያ አለመዘመን፣ በአገልግሎት መስጫዎች የኤሌክትሪክ ሲስተም መቆራረጥ፣ የሰራተኞች ስነምግባር ችግር፣ የደንበኞችን የስልክ ጥሪዎች አለማንሳትና የመሰላቸት ችግሮች መስተዋላቸው ተገልጿል።
የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የተቋቋመው ፎረም አንፃራዊ መሻሻሎች እንዳመጣ በመድረኩ ተነስቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ነጋሽ ባጫ ችግሮችን ለመፍታት በየጊዜው እየታረሙ በመሄድ ላይ ናቸው ብለዋል።
በበጀት አመቱ 11 ሺህ 291 የመንገድ ዳር መብራት ፖልና ሌሎች ጥገናዎች መካሄዳቸውን የሚያሳይ ሪፖርት ቀርቧል።
በአፈወርቅ እያዩና ትዝታ ደሳለኝ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
93
Engagements
Boost Post
87
3 Comments
3 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.