Fana: At a Speed of Life!

በዋግ ኽምራ ግንባር የተሰለፉ የአማራ ሚሊሻ አባላት አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ መዘጋጀታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዋግ ኽምራ ግንባር የተሰለፉ የአማራ ሚሊሻ አባላት አሸባሪውን ትህነግ ለመደምሰስ መዘጋጀታቸውን ገለጹ።
የትህነግ አሸባሪ ቡድን የአማራ ሕዝብን ጀግንነት ዘንግቶ ድንበር ተሻግሮ ትንኮሳ በመፈጸሙ አይቀጡ ቅጣት ልንቀጣው ነፍጣችንን አንግበን መጥተናል ብለዋል።
የአማራ ሕዝብ ከአሸባሪው ትህነግ ጋር በጀግንነት ተዋግተን ህልውናችንን እንድናስከብር በክብር ሲሸኙን ትህነጎች ግን ሕጻናትን እና አረጋውያንን በጦር ሜዳ ከኛ ጋር በማሰለፍ በሕግ ብቻ ሳይሆን በፈጣሪ ዘንድም የማይወደድ ሥራ በመሥራት ላይ ይገኛሉ ነው ያሉት።
ከአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር÷ ከምሥራቅ ጎጃም ዞን ከመጡ ሚሊሻዎች እና ከጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል ጋር በጋራ ሆነን ትህነግን ለመደምሰስ ዝግጅታችንን አጠናቀናል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
በተያያዘም የቀድሞ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የተደረገላቸውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ህልውና ማስከበር ዘመቻ እየተቀላቀሉ ሲሆን÷ በሀገር ላይ የሚቃጣን ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.