የሀገር ውስጥ ዜና

በመተከል ዞን ከ5 ሚሊየን በላይ ችግኞች እየተተከሉ ነው

By Alemayehu Geremew

July 16, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ5 ሚሊየን በላይ ችግኞች እየተተከሉ ነው፡፡

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የመተከል ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አበበ እንድሪስ እንደገለፁት በዚህ ዓመት በዞኑ በሚገኙ አራት ወረዳዎች 5 ሚሊየን 500 ሺህ ለምግብነት የሚውሉ ምጣኔ ሃብታዊ ጠቀሜታ ያላቸው እና ሀገር በቀል የሆኑ ችግኞች ይተከላሉ፡፡

ኃላፊው እስካሁን በዳንጉር እና ፓዊ ወረዳዎች ከ250 ሺህ በላይ ችግኞች መተከላቸውን ጠቁመዋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ72 ሚሊየን በላይ ችግኞች ለመተከል ዝግጅት መደረጉም ታውቋል።

በዘንድሮው ”የኢትዮጵያን እናልብሳት” የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመላ ሃገሪቱ ከ6 ቢሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ተግባራዊ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ እንደሚገኝም ኢዜአ ዘግቧል፡፡