Fana: At a Speed of Life!

የህወሓት አሸባሪ ቡድን ለመመከት የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ የጋምቤላ ከተማ ወጣቶች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህወሓት አሸባሪ ቡድን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የጀመረውን ጦርነት ለመመከት የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ በጋምቤላ ከተማ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ወጣቶች ገለጹ።
ወጣቶቹ አሸባሪው የህወሓት ቡድን የመንግሥትን የተናጠል የተኩስ አቁም ባለመቀበል እየፈጸመ ያለውን የሽብር ተግባር እንደሚያወግዙ አስታውቀዋል።
ወጣት ኦባንግ ኮመዳን እንዳለችው፤ አሸባሪው ቡድን በትግራይና አጎራባች ክልሎች እያካሄደ ያለው የሽብር ወንጀል የሚያሳፍር ነው።
አሸባሪው ቡድን ሀገር ለማፍረስ የሚያደርገውን እኩይ ተግባር ለመቀልበስ እንደ ሌሎቹ የኢትዮጵያ ወጣቶች ሁሉ የዜግነት ግዴታዋን ለመወጣት መዘጋጀቷን አስታውቃለች።
የጥፋት ቡድኑ ባለፉት 27 ዓመታት በኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸመው ግፍና በደል ሳያንሰው አሁን ተጨማሪ ጥፋት እያደረሰ መሆኑን የገለጸው ደግሞ ወጣት ኃይሌ አራጌ ነው።
ባለፈው ጥቅምት ወር በሀገር መከለካያ ሰራዊት ላይ ከፈፀመው ጥቃት በተጨማሪ በማይካድራና ሌሎች አካባቢዎች በአማራ ህዝብ ተጨማሪ ጉዳት ማድረሱን እንደቀጠለበት ተናግሯል።
ቡድኑ በህዝቡ ላይ የሚፈጽመውን ጥቃትና ሀገር የማፍረስ ዓላማውን ለማክሸፍ የኢትዮጵያ ወጣቶች በአንድነት እንዲነሱ መልዕክት አስተላልፏል።
ወጣት ኮንግ ጋድቤል በበኩሉ፤ አሸባሪው ቡድን ከ20 ዓመታት በላይ የትግራይ ሕዝብና ድንበርን ሲጠብቅ የቆየውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ያጠቃ ከሃዲ መሆኑን በመግለጽ ድርጊቱን ኮንኗል።
ሀገር ለመበታተን የመጣን ኃይል ቁጭ ብሎ እንደማያይ የገለጸው ወጣቱ፤ ከመንግሥት ጎን በመሆን የዜግነት ግዴታውን ለመወጣት መዘጋጀቱን ገልጿል።
ኢትዮጵያን አፍርሳለሁ ብሎ የተነሳውን ኃይል ለመመከት ኢትዮጵያዊን መነሳት አለብን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.