Fana: At a Speed of Life!

የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ  መግለጫ  ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ  መግለጫ  ሰጥቷል፡፡

ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክልሉን ህዝብ በማቀናጀት በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጣውን የውስጥና የውጪ ትንኮሳን ለማክሸፍ ዝግጁነቱን ይገልፃል፡፡

ወትሮም ቢሆን ለሰልጣን እንጂ ለሀገርና ህዝብ ግድ የሌለው አሸባሪው የህውሃት ቡድን ከለውጡ ጅማሮ አንስቶ ሀገሪቱን እንደሚያሻግር ተስፋ የጣሉበትን ሀገራዊ ለውጥ ለመቀልበስ አንዴ ከውስጥና ውጪ ሆነው የኢትዮጵያን ውድቀት ከሚመኙ አካላት ጋር በማበርና በማሰለፍ ሀገሪቱን ለመበታተን ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።

ጁንታው ሙከራዎች ሁሉ አልሳካ ሲለው የሀገራችንን ምልክት የሉአላዊነታችን ደጀን የአፍሪካውን መመኪያ በሆነው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ጭካኔ በተሞላበት መልኩ በማጥቃት ከሀዲነቱን ዳግም አስመሰከረ።

ሆኖም መላው ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነው ከሀገር መከላከያ እና ከክልል የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ጫካ ለመግባት ተገዶ እና በህዝብ መሀል ተሰግስጎ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ሲፍጨረጨር ቆየ።

ሆኖም መንግስት የክልሉ በሁኔታው የተጎዳው የክልሉ ህዝብ ሰብአዊ ድጋፍ በበቂ ደረጃ ተደራሽ እንዲሆን እና አርሶ አደሩም እርሻውን ከተኩስ ድምፅ ነፃ ሆኖ እንዲከውን ታሳቢ በማድረግ የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ ለሕዝብ ጥሩ የጥሞና ግዜ የፈጠረ መሆኑን አምኖ ስደግፍ ቆይቷል፡፡

ሆኖም ግን ሕወኃት/ጁንታ ለሕዝብ ጥቅም ተብሎ ለተደረገዉ ጥሪ ወደ ጎን በመተው ህዝብ ቦታ እንደሌለዉ ጦርነት በማወጅና ትንኮሳ በመፈፀም በግልፅ በማሳየት ዛሬም እንደ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ ይገኛል።

ጁንታው በተባበሩት መንግስታት የወጣዉን የሕፃናት መብት ድንጋጌ በመጣስ የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናትን ለጦርነት በመማገድ ላይ ይገኛል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አዛዉንቶችን፡ እናቶችንና የሐይማኖት አባቶችን በማሰለፍ በእልቂታቸዉ የጀግንነት አክሊል ለመድፋት ይሞክራል፡፡

በመሆኑም በተለይም በአሁኑ ወቅት መላው ኢትዮጵያውን ከመቼውም ጊዜ በላይ  በአሸባሪው ቡድን በሚነዙ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ሳንወናበድ፤ ውስጣዊ አንድነታችንን በማጠናከር፤ እርስበእርስ   በመመካከርና በመደጋገፍ፤  የተቃጣብንን አገራዊ ጥቃት በህብረትና በአንድነት፤ እንደ አንድ ልብ ሆነን የተደቀነብንን ሀገር የማፍረስ ተግባር መመከት ይገባናል።

የክልላችን ህዝብና መንግስትም በሀገር ህልውና ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመመከት እንደወትሮው ያልተቆጠበ ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያደር ያረጋግጣል።

ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ህብረት ታፍራና ተከብራ ትኖራለች!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!

የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት

ሐምሌ 2013

ሀረር

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.