ዓለምአቀፋዊ ዜና

የአፍጋን መንግስት በታሊባን ላይ አዲስ የጥቃት ዘመቻ መክፈቱን ገለጸ

By ዮሐንስ ደርበው

July 16, 2021

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2013 (ኤፍ  ቢ ሲ) የአፍጋኒስታን መንግስት በታሊባን ላይ አዲስ የጥቃት ዘመቻ መክፈቱን ይፋ አድርጓል፡፡

ዘመቻው ታሊባን የተሰኘውን ታጣቂ ቡድን ከሀገሪቱ ድንበር ለማስወጣት ያለመ መሆኑን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡

በዚህ መሰረትም አሁን ላይ በታሊባን ቁጥጥር ስር የሚገኙ ቁልፍ እና ስትራቴጂክ ስፍራዎችን ለማስለቀቅ መታቀዱ ነው የተገለጸው፡፡

በተለይም በደቡብ ካንዳሃር ግዛት የምትገኘውን ወሳኝ ድንበር ለማስለቀቅ ሁሉም  የጸጥታ  ሃይሎች በቅንጅት እንደሚሰሩ  ባለስልጣናቱ ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ የአሜሪካ ወታደሮች ከአፍጋኒስታን መውጣታቸውን ተከትሎ የታሊብን ታጣቂ ቡድን አባላት በርካታ ግዛቶችን መቆጣጣር መጀመራቸው በዘገባው ተመላክቷል፡፡

በዚህ ምክንያትም በአፍጋኒስታን መንግስት እና በታሊባን መካከል የሚደረገው ጦርነት እንደገና ማገርሸቱ እየተነገረ ነው፡፡

ምንጭ÷ ሺንዋ