Fana: At a Speed of Life!

ህወሃት የሽብር ተግባሩን ሊመኝ ይችላል እንጂ በፍጹም ተግባራዊ ሊያደርግና ሊያሳካ አይችልም- የደቡብ ክልል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህወሃት የሽብር ተግባሩን ሊመኝ ይችላል እንጂ በፍጹም ተግባራዊ ሊያደርግና ሊያሳካ እንደማይችል የደቡብ ክልል ገለፀ፡፡
ክልሉ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሸጥቷል ፡፡
ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከህወሀት የሀገር ክህደት ተግባራዊ እርምጃ በኋላ መንግስት ሲያካህድ የቆየዉ የህግ ማስከበር ዘመቻ የተናጥል የተኩስ አቁም እርምጃ ሲወስድ ህዝቡ በጦር እንቅስቃሴ ሳይረበሽ የኸር እርሻውን የሚያከናውንበት ሁነታ እንዲፈጠርለት እና የሰብአዊ እርዳታና ድጋፍ አቅርቦ በነፃነት የሚከናወንበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲባል ነዉ፡፡
ይሁን እንጅ አሸባሪው ቡድን በመንግስት የተወሰደዉን የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት ተጠቅሞ ከስህተቱ ከመማር ይልቅ ኢትዮጵያን የማፈራረስ የጋራ ዓላማ ካላቸው ሃይሎች ጋር በመተባበር ሀገራችንን ለማፍረስና ሉአላዊ ክብሯ እንዲደፈር እየሰራ ይገኛል፡፡
ይህ የሽብር ቡድን ለዚህ እኩይ አላማው፤እድሜያቸዉ ያልደረሱ ህፃናትን፤ የሃይማኖት አባቶችን፤ ሴቶችን ጨምሮ በግዳጅ በጦርነት በመማገድ ለሃገራችን ብቻ ሳይሆን ለአለም አቀፍ ህግጋት ተፈጻሚነት ደንታ የሌለው ጨካኝ ቡድን መሆኑን በይፋ እያስመሰከረ ይገኛል፡፡
አሸባሪው ሕወሃት ኢትዮጵያን በመራበት ዓመታት ሁሉ ህዝብ አንድ እንዳይሆን ሲሰራ መቆየቱ ይታወቃል፤ በብሔር፣ በቋንቋ፣በኃይማኖትና በተለያየ መነሻ ሲከፋፍል መቆየቱም እደዝሁ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነዉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አሁን መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብና ሀገር ላይ የከፈተዉን ጦርነት የሀገሪቱ ዉስን ክፈሎች ለማስመሰል በሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳዉ ሲዳዳዉ ይደመጣል፡፡
የክልላችን ህዝብና መንግስት የአሸባሪ ቡድኑን የሀገር ክህደት እኩይ ተግባር አጥብቆ ያወግዛል፣እያደረሰ ያለው ጥቃት ከአንድ የህዉሀት አሸባሪ ቡድን ብቻ አለመሆኑንና የተቃጣዉም በአንድ አካባቢ ላይ ሳይሆን በሀገራችን ህልዉናና ሉአላዊነቷ ላይ መሆኑን መላዉ የክልላችን ህዝብ በሚገባ ይገነዘባል፡፡
ህዉሀት የሽብር ተግባሩን ሊመኝና ሊሞክር ይችላል እንጂ በፍጹም ተግባራዊ ሊያደርግና ሊያሳካ አይችልም ምክንየቱም ሀገራችን በልጆቿ ታፍራና ተከብራ የኖረች፣ በሉአላዊነቷ የማይደራደር ህዝብና ታሪክ ያላት ሃገር ነች፡፡
መንግስት የአሸባሪ ቡድኑ እኩይ ተግባር ላይ የሚወስደዉን እርምጃ የክልላችን መንግስት ከዚህ ቀደምም እየደገፈ ይገኛል ይህንኑ በምያስፈልግ መጠን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
መላዉ የክልላችን ህዝቦች ለሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ድጋፍ ጎን ለጎን የአካባቢያችንን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ፣ ከፀጥታ ሃይሉ ጋር በትብብርና በቅርበት በመስራት፣ ለህዳሴ ግድባችን ድጋፋችንን በማጠናከር፣ አገራዊ ሃላፊነታችንን በንቃት እንድንወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
እኔ ያልመራኋት ሀገር ትፈርሳለች የሚል እምነት ያለው አሸባሪው ጁንታ የሀገራችንን ህልውና ለመናድ እያደረገ ያለው ጥረት በህዝባችን የጋራ ትግል እንደሚከሽፍ ጥርጥር የለንም፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.