Fana: At a Speed of Life!

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ በዝናብ እጥረት ሳቢያ ለችግር ለተጋለጡ አርሶ አደሮች በአጭር ጊዜ የሚደርሱ ዝርያዎችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ ዩኒቨርስቲ በዝናብ እጥረት ሳቢያ ለችግር ለተጋለጡ ለምስራቅ ሐረርጌ ዞን ወረዳ አርሶ አደሮች በአጭር ጊዜ የሚደርሱ ዝርያዎችን ድጋፍ ማድረጉ ተገለፀ፡፡
የክረምቱ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ባለመዝነቡ ለምግብ እጥረት ችግር ሊዳረጉ ይችላሉ ተብለው ለተለዩ ዘጠኝ ወረዳዎች ነው የሐረማያ ዩኒቨርስቲ በአጭር ጊዜ የሚደርሱ 460 ኩንታል የእህልና የአትክልት ዘሮችን በድንገተኛ የዘር ስርጭት መርሃ ግብር ያከፋፈለው፡፡
ቦሎቄ፣በቆሎ፣ማሽላ፣ስንዴ፣ ሽንብራና የአትክልት ዘሮች ለዘጠኙ ወረዳዎች ለሚገኙ 7ሺህ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች ተሰጥቷል፡፡
በዝናብ እጥረቱ ሳቢያ የዘሩት ለጠፋባቸው ከ1 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ደግሞ 14 ኩንታል ሦስት አይነት የምርጥ ዘር ዝረያዎች ተሰጥቷቸዋል።
የሐረማያ ዩኒቨርስቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጀይላን ወልዪ ዩኒቨርስቲው የአካባቢው አርሶ አደሮች በዝናብ እጥረት ሳቢያ የዘሩት ዘር ከመሬት ውስጥ ሳይወጣ በመጥፋቱ ለምግብ እጥረት እንዳይዳረጉ በአጭር ጊዜ የሚደርሱ የእህልና የአትክልት ዘሮችን በማከፋፈል ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት የህዝብ አጋርነቱን ማሳየቱን አስታውቀዋል።
የምስራቅ ሐረርጌ ዞን የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ጽህፈት ቤት ምክትል በኃላፊ አቶ ጌታሁን ንጋቱ በበኩላቸው ÷በዞኑ በበልግ ወቅት በዘር ከተሸፈነው 47ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ በዝናብ እጥረቱ ሳቢያ 81 በመቶ ምርት በመጥፋቱ አርሶ አደሩ ለምግብ እጥረት ሊዳረግ እንደሚችልና የመኸር ዝናብም ወቅቱን ጠብቆ ባለመዝነቡ አርሶ አደሩ ለምግብ እጥረት ሊዳረግ እንደሚችል በተደረገ በዳሰሳ ጥናት መረጋገጡን ተናግረዋል፡፡
በተሾመ ኃይሉ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.