ዓለምአቀፋዊ ዜና

ፋውዚያ ዩሱፍ በፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር ለሶማሊያ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቀረቡ

By Alemayehu Geremew

July 16, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያ የቀድሞ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ፋውዚያ ዩሱፍ ሀጂ አደም በሶማሊያ በሚካሄደው ቀጣይ ምርጫ ለፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር የዕጩነት ጥያቄ አቀረቡ፡፡

የሀገሪቷ ምርጫ ቦርድም ጥያቄያቸውን ከተቀበለው በሶማሊያ የምርጫ ታሪክ ለከፍተኛ አመራርነት ጥያቄ ያቀረቡ ሁለተኛዋ ሴት ይሆናሉም ነው የተባለው፡፡

በፈረንጆቹ 2004 አሻ አህመድ አብደላ በሀገሪቷ ፓርላማ ውስጥ ለከፍተኛ አመራርነት ተወዳድረው ያላለፉ የመጀመሪያዋ የሴት ዕጩ እንደነበሩ ዘ ኢስት አፍሪካን አስታውሷል፡፡