Fana: At a Speed of Life!

ለተፈናቃዮችና ህግ ለማስከበር ለተሰማሩ ከ135 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በአማራና በአፋር ክልል ለሚገኙ ተፈናቃዮችና ህግን በማስከበር ላይ ላሉ አካላት የሚውል ከ135 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል ።
ድጋፉ ህግን ለማስከበርና ኮንትሮባንድን ለመከላከል እየተሰራ ባለው ስራ በተለያዩ ጊዜ የተያዙ ቁሳቁሶች ፣አልባሳትና ምግብ ነክ መሆናቸው ተገልጿል ።
ለክልሎቹ የተደረገው ድጋፍ በተለያየ ጊዜ ላጋጠሟቸው ሰዉ ሰራሽና መሰል አደጋዎች እገዛ መሆኑን የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ተናግረዋል ።
በዚህም ለአማራ ክልል ከ87 ሚሊየን ብር በላይ እንዲሁም ለአፋር ክልል ከ52 ሚሊየን ብር የሚገመት አልባሳት ምግብና ምግብ ነክ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉ ታውቋል፡፡
ድጋፍን የየክልሎቹ ተወካዮች የተቀበሉ ሲሆን ÷ስለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዉ ድጋፉ ለሚያስፈልጋቸዉ አካላት በትክክለኛው መንገድ በማስረከብ ኃላፊነታቸዉን እንደሚወጡ ገልፀዋል ።
በብስራት መንግስቱ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.