Fana: At a Speed of Life!

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ.ም የተመደቡ 5 ሺህ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ 5 ሺህ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲው መግባት ጀምረዋል።
ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲው ሲደርሱ የአካባቢው ህብረተሰብ፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና ነባር ተማሪዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አዲስ ገቢ ተማሪዎች በተደረገላቸው አቀባበል መደሰታቸውን ገልፀው÷ በቆይታቸውም ትምህርታቸው ላይ ትኩረት አድርገው ለመማር መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።
የአካባቢው ማህበረሰብ አባላትም ተማሪዎቹን እንደ ልጆቻቸው በማየት እንደሚንከባከቡና እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡
በተሾመ ኃይሉ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.