Fana: At a Speed of Life!

ለሴካፋ ውድድር የእንኳን ደህና መጣችሁና የእራት ግብዣ መርሃ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሴካፋ ውድድር የእንኳን ደህና መጣችሁና የእራት ግብዣ መርሃ ግብር በባህር ዳር ከተማ ተካሄደ፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ ኢትዮጵያ የእግርኳስ የፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ፣ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የሴካፋ ውድድር ብሔራዊ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አበበ ገላጋይ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በመድረኩ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የእግርኳስ መድረክ ላይ ያላትን ተፅእኖ አውስተው ተጋባዥ ሀገራት በባህር ዳር ከተማ በሚቆዩበት ጊዜ ጥሩ ቆይታ እንደሚኖራቸው ገልፀው ኢትዮጵያ በእግርኳሱ ብቻ ሳይሆን በሌላም መንገድ ከሌሎች ሀገራት የተለየ ባህል፣ ታሪክ እና ወግ ያላት እንዲሁም በእንግዳ ተቀባይነቷ የተመሰገነች መሆኗን አውስተዋል፡፡
በመጨረሻም ለውድድሩ ተሳታፊ ሀገራት የማስታወሻ ስጦታ መበርከቱን ከኢትዮጵያ እግር ኳሽ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.