የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ እያካሄደ ነው

By Meseret Awoke

July 17, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 8ኛ ዓመት 3ኛውን መደበኛ ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል፡፡

ምክር ቤቱ በሚያካሂደው መደበኛ ጉባኤ የበጀት ዓመቱ የማጠቃለያ ሪፖርት በምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እንደሚቀርብ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩን የኦዲት ሪፖርት ለምክር ቤት የሚቀርብ ሲሆን የ2014 በጀት ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!