Fana: At a Speed of Life!

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 237 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ከማል አብዱራሂም እደገለጹት÷ በነገው ዕለት የሚመረቁት በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ለ8ተኛ ጊዜ የሰለጠኑ 2 ሺህ 237 ተማሪዎች ናቸው።
ዩኒቨርሲቲው በተያዘው ዓመት የኮሮና ቫይረስን ጫና ተቋቁሞ ሲያስመርቅ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ በቆይታቸው “እየገነባን እንማራለን፤ እየተማርን እንገነባለን” የሚለውን መሪ ቃል በመከተል ትምህርታቸውን በሰላም ማጠናቀቃቸው እንደመልካም ተሞክሮ የሚወሰድና የሚያስመሰግናቸው መሆኑን አውስተዋል።

በማስረሻ ፍቅሬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.