የሀገር ውስጥ ዜና

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው

By Meseret Awoke

July 17, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 237 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ከማል አብዱራሂም እደገለጹት÷ በነገው ዕለት የሚመረቁት በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ለ8ተኛ ጊዜ የሰለጠኑ 2 ሺህ 237 ተማሪዎች ናቸው። ዩኒቨርሲቲው በተያዘው ዓመት የኮሮና ቫይረስን ጫና ተቋቁሞ ሲያስመርቅ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ በቆይታቸው “እየገነባን እንማራለን፤ እየተማርን እንገነባለን” የሚለውን መሪ ቃል በመከተል ትምህርታቸውን በሰላም ማጠናቀቃቸው እንደመልካም ተሞክሮ የሚወሰድና የሚያስመሰግናቸው መሆኑን አውስተዋል።

በማስረሻ ፍቅሬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!