Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት የትግራይ ህጻናትን በሀሽሽ አዕምሯቸውን አደንዝዞ ለጦርነት እየማገደ ነው – ዶ/ር አረጋዊ በርሄ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት የትግራይ ህጻናትን በሀሽሽ አዕምሯቸውን አደንዝዞ ለጦርነት እየማገደ ነው ሲሉ የትግራይ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበርና የህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ገለጹ፡፡
አሸባሪው ህወሓት የትግራይ ህጻናትን ለእኩይ ተግባሩ በጦርነት ማሰለፉ የጀመረው ዛሬ ሳይሆን ከትጥቅ ትግል ወቅት አንስቶ እንደሆነ ነው ዶክተር አረጋዊ በርሄ ያስታወቁት፡፡
በአሁኑ ወቅት ሕጻናቱ አሸባሪውን ህወሓት እየተቀላቀሉት የሚገኙት አውቀውት፣ እኩይ አላማውንም ተረድተው ሳይሆን የነገ ተስፋቸውም ስለጨለመባቸው፣ በተዛባ ፕሮፖጋንዳ ልባቸውን ስላሸፈተው እና ሀሺሽ እየሰጠ ከአዕምሯቸው ውጪ ስላደረጋቸው ነው ሲሉም አብራርተዋል፡፡
ዶክተር አረጋዊ አሸባሪው ህወሓት የትግራይ ህጻናትን ለጦርነት ማሰለፍ የጀመረው ዛሬ ሳይሆን ከትጥቅ ትግል ወቅት እንስቶ እንደነበርም አስታውሰዋል፡፡
በዚህም በርካታ ሕጻናትን ያለእድሜያቸውና እውቀታቸው በጦርነት እንዲማገዱ አድርጓል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
በተጨማሪም ህዝቡና ጁንታው ምንም ግንኙነት እንደሌላቸውና ጁንታው ለግል ጥቅሙ ብቻ እየተሯሯጠ መሆኑን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሚገባ እንደሚያውቅም ገልፀዋል፡፡
ጁንታው ህጻናቱን ከአቅማቸው በላይ የጦር መሳሪያ አሸክሞ እድሜያቸው ወደማይፈቅደው ጦርነት ማስገባቱ ዓለም አቀፍ ወንጀል መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ዛሬ ዓለም አቀፉ ህብረተሰብ በተለይም ስለ ህጻናት መብቶች ያገባናል የሚሉ አካላት አይተው ዝም እንዳሉ ያመለከቱት ዶክተር አረጋዊ፥ ውሎ ሲያድር ቡድኑ በዚህ ኢ-ሰብዓዊ ስራው ከተጠያቂነት እንደማያመልጥ አመልክተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.