ሽብርተኛውን ትህነግ ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸዉን የአዲአርቃይ ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሽብርተኛውን ትህነግ ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸዉን የአዲአርቃይ ወረዳ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
የአዲአርቃይ ወረዳ ነዋሪዎች እንደገለፁት፥ ሽብርተኛው የትህነግ ቡድን ትንኮሳ መጀመሩን ተከትሎ በመደራጀት የአካባቢያቸዉን ሰላም ለማስጠበቅ በተጠንቀቅ ይገኛሉ፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ግዳጅ ቀጣና ለተሰማራዉ የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ ስንቅ እያቀረቡ እንደሆነ ገልፀው፥ በቀጣይም የሕይወት መስዋእትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸዉን አስታውቀዋል፡፡
የአዲአርቃይ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እሸቴ መልኬ በበኩላቸው የወረዳዉ ሕዝብ ለዘመቻዉ እያደረገ ያለዉ ድጋፍ ሰፊ መሆኑን ገልጸዉ፥ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ዋና አስተዳዳሪዉ አክለውም፥ የወረዳው ሕዝብ ሽብርተኛውን የትህነግ ቡድን ከአማራ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻ እና ሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ለመደምሰስ ዝግጁ ነዉ ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!