Fana: At a Speed of Life!

የጨፌ ኦሮሚያ የሁለተኛ ቀን ውሎ ቀጥሏል

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአፈጻጸም ሪፖርት በማዳመጥ ውሎውን ቀጥሏል፡፡
የፍርድ ቤቱ ፕሬዚደንት ጋዛሊ አባሲማል ሪፖርቱን ለጨፌ አባላት ያቀረቡ ሲሆን፥ የክልሉ ፍርድ ቤቶች አፈጻጸም 94ነጥብ 68በመቶ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይህ አፈጻጸምም በፍርድ ቤቶቹ ታሪክ ከፍተኛ አፈጻጸም ሆኖ መመዝገቡን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡
በ2014 ዓ/ም የሃሰት ምስክር እና የሃሰት ክስን ከመሰረቱ ለማስቀረት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም ነው የገለጹት፡፡
በተጨማሪም የኦሮሚያ የባህል ፍርድ ቤት በዘንድሮ ዓመት ስራ ላይ ለማዋል በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡
በዳግማዊ ዴክሲሳ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.