Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን የፖሊስ መኮንኖች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መርሃ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 476 የፖሊስ መኮንኖች አስመርቋል።
ሠልጣኞቹም በፖሊሰ ሳይንስ፣ በስነ-ወንጀልና ወንጀል ፍትህ፣ በነርሲንግ እንዲሁም በፖሊስ መኮንንነት ዘርፍ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።
ዩንቨርስቲው ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ተማሪዎችንም ማስመረቁ ታውቋል።
ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች የላቀ ውጤት ላመጡ ተመራቂ መኮንኖችም ሽልማት መስጠቱን ኢዜአ ዘግቧል።
ዩንቨርስቲው ከተቋቋመ 74 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፥ በቅርቡም ከኮሌጅነት ወደ ዩንቨርስቲ ማደጉ ይታወሳል።
በሰንዳፋበተካሄደው የምርቃ ስነ-ሰርዓቱ ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ደመላሽ ገብረሚካኤልን ጨምሮ ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች ተገኝተዋል።

ምንጭ÷ኢዜአ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.