Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ከተማ ሚሊሻ አባላት የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ እና ዘመቻ ለህልውና ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የጎንደር ከተማ ሚሊሻ አባላት የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ እና ዘመቻ ለህልውና ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሚሊሻ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ወረታው አቡሃይ እንደተናገሩት፥ የሚሊሻ ኃይላችን የሚሰጠውን ማንኛውም ተልዕኮ ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል። ሃላፊው አክለውም ጁንታው ኢትዮጵያን ማፍረስ አንደማይችል ገልፀዋል።
የሚሊሻ አባላቱም የከተማችን ሰላም ከማስጠበቅ በተጨማሪ የጁንታውን ኃይል ለመመከት ዝግጁ እንደሆኑ መግለጻቸውን ከጎንደር ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.