Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካይ አቱዋል ካሬ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱም የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል በተባበሩት መንግሥታት የተጫወተውን ሚና አስመልክቶ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በአቢዬ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ምንም የተለያዩ ችግሮች ቢገጥሙትም ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን አይነተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑንም ነው የተናገሩት ።
ኢትዮጵያ ለተባበሩት መንግስታት ቀጣይ ድጋፍ እንደምታደርግ ያረጋገጡት አቶ ደመቀ መኮንን፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካዩ አቱዋል ካሬ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል በተመድ የሰላም ማስከበር ተልእኮ ውስጥ እያበረከተ ያለውን ሚና አመስግነዋል።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአስቸጋሪው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት አፈጻጸም ማድነቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገነነው መረጃ ያመለክታል ።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.