Fana: At a Speed of Life!

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤት በሚቀጥለው ዓመት ለጉብኝት ክፍት ሊሆን ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)እጅግ የተከበሩ የለም ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤት ጥገናው ተጠናቆ በሚቀጥለው ዓመት ለጉብኝት ክፍት እንደሚሆን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ገለጸ፡፡
የተከበሩ የአለም ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤት አብዛኛው የጥገና ስራ መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅትም የሙዚየም ግንባታው በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

የመኖሪያ ቤቱ ቀሪ ስራዎች በሚቀጥለው ዓመት ተጠናቀው ለጉብኝት ክፍት እንደሚሆን ኢፕድ ዘግቧል ፡፡

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው፥ እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ መኖሪያ ቤት በጥንቃቄ በመስራት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ በቅርስ ጥገና ዙሪያ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የጠቆሙት ረዳት ፕሮፌሰር አበባው÷ በላሊበላ እና ጎንደር ታሪካዊ ስፋራዎችን በተሻለ ሁኔታ ጠግኖ ወደሥራ ለማስገባት እየተንቀሳቀሱ እንደሆነም አንስተዋል፡፡
በተጨማሪም ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በቀጣይ ዓመት በዩኔስኮ ሊመዘገቡ የተቃረቡ በርካታ ባህሎች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል፡፡
ለአብነትም የጌዲዮን የባህል መልክአምድር አንዱ እንደሆነ አንስተው፥ በዩኔስኮ ለማስመዝገብም የፋይል እውቅናው ተጠናቆ ድምጽ እንደሚሰጥበት ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.