Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ዞን በዘንድሮው የመስኖ ልማት ከ1ሚሊየን ኩምታል በላይ የስንዴ ምርት መገኘቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  በጅማ ዞን በዘንድሮው የመስኖ ልማት ከ 1 ሚሊየን ኩምታል በላይ የስንዴ ምርት መገኘቱን የዞኑ ቡና፣ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በዞኑ 30 ሺህ 77 ሄክታር መሬት በመስኖ የለማ ሲሆን ÷ 1 ሚሊየን 300 ሺህ 200 ኩምታል የስንዴ ምርት መገኘቱ ነው የተገለፀው።

በመስኖ ልማቱ 31 ሺህ ኩምታል ምርጥ ዘርና 63 ሺህ ኩምታል ማዳበርያ ለአርሶ አደሮች መታደሉን ተመልክቷል።

ከዚህም በተጨማሪ የአርሶደሮችን ምርታማነት ለመጨመር 450 የውሃ ፓንፖችና 26 ትራክተሮች አገልግሎት ላይ መዋላቸውን የዞኑ ቡና፣ ግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኤሊያስ አንድሪያ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግሯል።

550 ሄክታር መሬት ላይ የነበረ የስንዴ ምርት በኮምባይነር መሰብሰቡንና የተቀረው በሠው ሃይል መሰብሰቡን ሃላፊው ጠቁመዋል።

አርሶ አደሮቹ ምርቱን የሚሸጡበት ዋጋ ከቦታ ቦታ ልዩነት አለው ያሉት ሃላፊው÷ በኩምታል ከፍተኛው 3 ሺህ 600 ብር እንዲሁም ዝቅተኛው 2 ሺህ 200 ብር እንደሚሸጥ ገልፀዋል።

በጅማ ዞን በዘንድሮው የመስኖ ልማት በአጠቃላይ 246 ሺህ አርሶአደሮች ተሳትፈዋል።

በሙክታር ጠሃ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.