Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሃት ለትግራይ ክልል የሚላከው የሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይጓጓዝ አስተጓጎለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለትግራይ ክልል የሚላከው የሰብዓዊ ድጋፍ በአፋር በኩል ወደ መቀሌ ሲጓጓዝ የአሸባሪው የህወሃት ቡድን አካባቢውን በከባድ መሳሪያ በመደብደብ መንገድ መዝጋቱ ተገለጸ።
መንግስት በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ በተገቢው መልኩ ለማዳረስ የተናጥል ተኩስ ማቆሙ ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበ መሆኑን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን መግለጹ ይታወቃል።
ዛሬ በአፋር ክልል በኩል ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችን የጫኑ 60 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እየተጓዙ ሳለ የአሸባሪው ህወሃት ቡድን ተኩስ በመክፈት እንዳይጓጓዝ መንገድ መዝጋቱን ምንጮች ለኢዜአ የላኩት መረጃ ያመለክታል።
ለትግራይ ክልል የሚሂድ የእርዳታ ቁስና ምግብ ነክ የሆነ ተፍትሾ እንዲያልፍ ሰርዶ 60 እና ሚሌ ኬላዎች ላይ እየተሰራ ቢሆንም፤ አሸባሪው ህወሃት በዞን አራት ያሉ የአፋር ፖሊስና ልዮ ሀይል አባላትና ማህበረሰብን በከባድ መሳሪያ እየደበደበ “ወደ ትግራይ የሚሄድ እርዳታ አይኖርም” በማለት ሰርዶ ኬላ ላይ መዝጋቱን ከአካባቢ የተገኙ ምንጮች ለኢዜአ ገልጸዋል።
ህወሃት የተኩስ አቁም ውሳኔውን “አልቀበልም” በማለት ግጭቱን ወደ አፋር ክልል ለማስፋት እየሰራ መሆኑም ታውቋል።
በቅርቡም መንግስት ሁኔታዎች በማመቻቸቱ ለክልሉ ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ 61 ከባድ ተሽከርካሪዎች ትግራይ ክልል መድረሳቸው ይታወሳል።
ከዚህ ውስጥ 34ቱ ምግብ ነክ ድጋፎችን የጫኑ ሲሆን፤ 26 ተሽከርካሪዎች ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን የጫኑ ሲሆኑ፤ ከ47 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ የጫነ አንድ ከባድ ተሽከርካሪም መቀሌ መድረሱ ተዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of outdoors
0
People Reached
39
Engagements
Distribution Score
Boost Post
32
2 Comments
5 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.