የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ከሳኡዲ አረቢያ ውጭ  ጉዳይ  ሚንስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ

By Meseret Demissu

July 17, 2021

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ ከሳኡዲ አረቢያ ውጭ  ጉዳይ  ሚንስትር ዴኤታ አምባሳደር ተሚሚ አል-ደውሰሪ ጋር  ውይይት አካሂደዋል።

በውይይታቸውም 42 ሺህ ዜጎችን ወደ አገር የመመለስ ዘመቻ ሥራ መጠናቀቅን፣ በማቆያ ማእከላትና በእስር ቤቶች ያሉ ዜጎችን በቀጣይ ወደ አገር መሸኘት በሚቻልበት መንገድ፣ በማቆያ ማእከላትና በእስር ቤቶች ያሉ ዜጎችን አያያዝን እንዲሁም  የሳኡዲ አረቢያ መንግስት  በህገ ወጥ መንገድ የገቡ  ዜጎችን በሚመለከት የሚያካሂደውን የእስር ዘመቻ የተመለከተ ምክክር አድርገዋል።

በተጨማሪም ወደ አገር መመለስ ፈልገው በተለያዩ ምክንያቶች ወደ አገር መመለስ ያልቻሉ በራሳቸው የትኬት ወጪ  ያለምንም እስርና ገንዘብ መቀጮ የሳኡዲ አረቢያ ምህረትን ተጠቅመው ወደ አገራቸው በሚመለሱበት ዙሪያ መክረዋል።

ምህረት ተደርጎላቸው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ  ጥያቄው ለሳኡዲ አረቢያ ንጉስ ሠልማን ቢን አብዱልአዚዝ  ቀርቦ ለኢትዮጵያውያን ምህረት አድርገዋል።

በቀጣይነት ኤምባሲው የምዝገባ መርሀ ግብር በመክፈት የጉዞ ሂደቱን እንደሚጀምር  በሪያድ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!