Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ በረራ ጀመረ

 

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ በረራ ጀመረ::

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዛሬ ወደ መቐለ በረራ ያደረገው ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ ነው።

ከአዲስ አበባ ስደሰት ሰዎችን ይዞ ወደ መቐለ የበረረው አውሮፕላን ንብረትነቱ የተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም መሆኑ ኢዜአ ከምንጮቹ መረጃውን አግኝቷል።

የመጀመሪያ በረራው የተካሄደው መንግስት ለትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ በአየር እንዲጓጓዝ በፈቀደው መሰረት ነው።

ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ የተደረገው በረራ ድጋፉ በምግብና ስነ-ምግብ አቅርቦት የሚሳተፉ በክልሉ ከሚገኙ ወረዳዊች መካከል በ21 ወረዳዎች ለሚሰሩ ሰራተኞች ደመወዝ ፣ ለስራ ማስኬጃ ለምግብ ቁሳቁስ መጫኛና ማውረጃ የሚውል ገንዘብ መሆኑ ምንጮች ጠቁመዋል።

ዛሬ አውሮፕላኑ ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል።

መንግስት በክልሉ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ በተለያዩ መስኮች በትኩረት የሰራ ሲሆን፤ ከጅቡቲ ወደብ ወደ ክልሉ ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ በርካታ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ አድርጓል።

መንግስት የሰብዓዊ ድጋፉን በአውሮፕላን ማከናወን ለሚፈልጉ አካላት ሲወጡም ሆነ ሲገቡ የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያን ብቻ እንዲጠቀሙ መወሰኑንም ይታወቃል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.