የሀገር ውስጥ ዜና

ጁንታዉ በተስፋ-መቁረጥ ስሜት በአፋር ክልል በሰዉና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል

By Tibebu Kebede

July 17, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጁንታዉ በተስፋ-መቁረጥ ስሜት የከፈተዉን ጥቃት ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ እልባት ለመስጠት የክልሉ ህዝብና መንግስት በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን የአፋር ክልል ሰላምና አስተዳደር ቢሮ ገለጸ::

ዛሬ ከጧቱ 2 ሰአት ጀምሮ ጁንታዉ በአፋር ክልል ፈንቲረሱ ዞን ያሎ ወረዳ በንጹሃን አርብቶአደሮች ላይ በከፈተዉ ድንገተኛ ጥቃት በሰዉና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

የቢሮዉ ሃላፊ አቶ ኢብራሂም ሁመድ ለኢዜአ እንደገለጹት ጁንታዉ በተሰፋ መቁረጥ ውስጥ ሆኖ ሀገር ለማተራመስ ቀን ከሌሊት ቢሰራም በህዝቦች የተባባረ ክንድ ግብአተ-መሬቱ የሚፈጸምበት ግዜ ቅርብነ ዉ።

ጁንታዉ ይህንን አውነት የገባዉ በሚመስል ሁኔታ በአፋር ክልል ያሎ ወረዳ ዛሬ ጧት 2ሰአት ጀምሮ በንጹሃን አርብቶ አደሮች ላይ ጥቃት ፈጽሟል ብለዋል።

በዚህም ለግዜዉ በውል ባይታወቅም ህጻናትና ሴቶችን ጨምሮ በአርብቶ አደሮች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆንም የተለያዩ የግለሰብ ቤቶችንም ጨምሮ ዝርፊያ ፈጽሟል።

ይህን ተከትሎ ወደ ስፋራዉ የደረሰዉ የክልሉ ልዩሃይልና የአካባቢዉ ህብረተሰብ የመከላከል እርምጃዎችን በመውሰድ የጁንታውን አላማ ማክሸፍ የተቻለ ቢሆንም አሁንም ጦርነት ጦርነቱ በአካባቢው መቀጠሉን አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!