Fana: At a Speed of Life!

ወደ ግዳጅ ቀጠና ለሚያመሩ የሀረሪ ክልል ልዩ ሀይል አባላት ሽኝት ተደረገ

 

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪውን ትህነግ ጁንታ ሀገር አፍራሽ ተግባርን ለማክሸፍ ወደ ግዳጅ ቀጠናው ለሚያመሩ የሀረሪ ክልል የልዩ ሀይል የፖሊስ አባላት የክልሉ መንግስት በዛሬው እለት የሽኝት ስነ-ስርአት አካሂዷል።

በሽኝት ስነ-ስርአቱ ላይ የተገኙት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ሀገራችን በዚህ ወቅት ከውስጥና ከውጭ የተጋረጠባትን ጫና ለመመከት በሚደረገው ትግል ተሳታፊ መሆን ታሪካዊ እድል መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

ለግዳጅ ተልዕኮ የምትሰማሩ የፖሊስ አባላትም በዚህ ልትኮሩ ይገባል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የተሟላ ስብእና እና ስነ ምግባር በመላበስ ህዝባዊነታችሁን እንድታረጋግጡ እንዲሁም የሚሰጣችሁን ሀገራዊ ተልዕኮ በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት እንድትወጡ ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ የአደራ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡

ለግዳጅ ተልዕኮ የተዘጋጁ የፖሊስ አባላትም በዚህ ታሪካዊ አጋጣሚ ተሳታፊ በመሆናቸው የተሰማቸው ደስታ ገልፀው ተልዕኮውን በስኬት ለማጠናቀቅ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

ለክልሉ ልዩ ሀይል በተዘጋጀው የሽኝት ስነስርአት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ; ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ; በክልሉ የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፋ አቶ አብዱጀባር መሀመድ እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎችና የፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች ተሳትፈዋል ሲል የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.