Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ 14 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሀረሪ ክልል ለታላቁ የህዳሴ ግድብ በአምስት ወር ከአስራ አራት ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ።
የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ዋንጫ በክልሉ ከጥር 27 ቀን 2013 ጀምሮ የነበረውን የአምስት ወራት ቆይታ አጠናቆ ለድሬዳዋ አስተዳደር አስረክቧል።
ዋንጫው በክልሉ ነበረው ቆይታ በከተማና በገጠር በሚገኙ ዘጠኙ ወረዳዎችና የተለያዩ የመንግስት ተቋማት ለግድቡ ገቢ ከማሰባሰብ ባሻገር ስለ ግድቡ ለህብረሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ መሰራቱን ተመላክቷል።
የዋንጫ ርክክቡ በተደረገበት ወቅት የሀረሪ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሚስራ አብደላ እንዳሉት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከህፃን አስከ አዋቂ በግድቡ ግንባታ ላይ አሻራውን ያኖረበትና ከተባበርን የማንችለው ነገር እንደሌለ ማሳያ እንዲሁም በብሄር ብሔረሰብና ህዝቦች መካከል አንድነትን ያጠናከረ የቀጣዩ ብልፅግናችን ማሳያ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ዋንጫው በሀረሪ ክልል በነበረው ቆይታ ሃያ ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እንደነበር የገለፁትና በአፈፃፀሙም አስራ አራት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን የገለፁት ደግሞ የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊና የታላቁ የህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ ናቸው።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በሀረሪ ክልል በነበረው ቆይታ ድጋፍ ላደረጉ ወረዳዎችና የተለያዩ ተቋማት እንዲሁም ባለሃብቶች ዋንጫና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
ዋንጫው በክልሉ የነበረውን ቆይታ አጠናቆ ወደ ድሬዳዋ አስተዳደር የተሸኘ ሲሆን ዋንጫውንም ወ/ሮ ሚስራ አብደላ የሀረሪ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳደር ለድሬዳዋ አሰወተዳደር ም/ከንቲባ ለአቶ አህመድ መሐመድ ቡህና ለሌሎች የካቢኔ አባላት አስረክበዋል።
በተሾመ ኃይሉ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.