Fana: At a Speed of Life!

ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ለሚንቀሳቀሰው የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል ሽኝት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ለሚንቀሳቀሰው የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል የሽኝት መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡
በመርሃ ግብሩ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ፣ የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅሕፈት ቤት ሀላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የክልሉ ካቢኔ አባላት ተገኝተዋል።
በሽኝት መርሃ ግብሩ አቶ ሙስጠፌ መሃመድ እንደገለፁት÷ ህዝባችንን ለዘመናት የጨፈጨፈው አሸባሪው የህወሃት ጁንታ ዛሬም ሀገር ለማፍረስ የጀመረውን ስራ ለመመከት የሶማሌ ልዩ ሀይል ዝግጁ ነው።
እንዲሁም ሰራዊቱ በድል እንደሚመለስ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።
በመጨረሻም በሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል ዋና አዛዥ ረዳት ኮምሽነር መሀመድ አህመድ መሪነት የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይል ወደ ግዳጅ ስፍራ ማቅናቱን ከሶማሌ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.