Fana: At a Speed of Life!

በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአገሪቷ የመጨረሻ ምሽግ እንጂ የአንድ ፖለቲካ ድርጅት ምሽግ አይደለም- ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአገሪቷ የመጨረሻ ምሽግ እንጂ የአንድ ፖለቲካ ድርጅት ምሽግ እንዳልሆነ የአገር መከላከያ የሰራዊት ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ ገለጹ።
ከሶስትና አራት አመታት በፊት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአቢዮታዊ ዲሞክራሲ የመጨረሻ ምሽግ እንጂ የኢትዮጵያ እንዳልነበረም ጠቁመዋል።
ሌተናል ጀነራሉ ይህን ያሉት ጦቢያ ፕሮግራም ላይ ሲሆን÷ በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአገሪቷ የመጨረሻ ምሽግ እንጂ የአንድ ፖለቲካ ድርጅት ምሽግ አይደለም ብለዋል።
የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለአገሪቷ ሁለንተናዊ ለውጥ የሚተጉባት ወቅት ላይ መሆኑን አመላክተው ይህም በመሰረታዊ ሀሳብ በመስማማት መሆኑን ጠቁመው 6ኛው አገራዊ ምርጫን እንደ ማሳያ አንስተዋል።
በአገሪቷ በህጋዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከስልጣን ይልቅ አገርን በማስቀደማቸው ምንጊዜም ክብር አለን ብለዋል።
በኢትዮጵያ ለዘመናት የነበረው ወታደራዊ አስተምሮ አገሪቷን ከሚመሯት ጋር የተቆራኘ ስለመሆኑ ያነሱት ሌተናል ጀነራል ባጫ ይህም ለመሪዎችና ለሃሳባቸው ታማኝ አገልጋይ ቢሆኑም አገራችንን ወራሪ ባጋጠማት ጊዜ ለህይወቱ ሳይሳሳ ማንኛውንም መሰዋትነት ከፍሎ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ጠብቆ መቆየቱን ተናገረዋል።
”ኢትዮጵያ የምትፈልገው የኢትዮጵያ ወታደር ነው ያሉት ሌተናል ጀነራል በጫ” ይህም ሆኖ የአገር መከላከያ ሰራዊት ከአመታት በፊት የነበረው ምሽግ ቀርቶ አገራዊ እይታና አንድነትን በሚያስጠብቅ ቅኝት መደራጀቱን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.