Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ በነገው ዕለት የሲቪል አቪየሽን አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ያፀድቃል

አዲስ አበባ፣ ጥር 18 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባ በነገው እለት ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ በነገው በስብሰባው የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የ2012 በጀት ዓመት የ6 ወር የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ያደምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ከዚህ ባለፈም የሲቪል አቪየሽን አዋጅን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚያፀድቅ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ነባሩ የሲቪል አቪዬሽን አዋጅ በቆየባቸው የትግበራ ዓመታት ውስጥ በህግ ያልተሸፈኑ አዳዲስ አስተሳሰቦች እና የቁጥጥር ስርአቶች በመኖራቸው የሰው ሀብት ስምሪትና የተፈላጊ ብቃት ተለዋዋጭነት መኖሩ አዋጁ እንዲሻሻል ረቂቁ መዘጋጀቱ በረቂቁ ተመልክቷል።
 
በተለይም ከዘርፉ ልዩ የስራ ባህሪ አንጻር የአቬዬሽን ዘርፉን ለመምራት እና ለመቆጣጠር፣ የበረራ ደህንነትን ለማረጋገጥ እና የአደጋ ስጋትን ለመቀነስ አለማቀፍ ድርጅቱ በየጊዜው የሚያወጣቸው ምክረ ሀሳቦች፣ ደረጃዎችና የተመረጡ አሰራሮች ተግባራዊነት ጋር በተያያዘ ክፍቶቶች በመፈጠራቸው እነዚህን ክፍተቶች በሚሞላና የወደፊት የኢንዱስትሪውን እድገት በጠበቀ መልኩ ለመደገፍ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ በትራንስፖርት ሚኒስቴር መዘጋጀቱ ተነግሯል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.