Fana: At a Speed of Life!

የኮሌራ በሽታን ለመከላከል እየተደረገ ያለው ርብርብ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሌራ በሽታን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ርብርብ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የበሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት የስራ ሂደት ባለቤት አቶ መና መኩሪያ ገለጹ።

በደቡብ ክልል በሚገኙ በተወሰኑ አካባቢዎች የተከሰተውን የኮሌራ በሽታ ለመከላከል በተደረገው ጥረት አሁን ላይ የችግሩ ጫና መቀነሱንም ተናግረዋል።

ወረርሽኙ ባልተከሰተባቸው አጎራባች ወረዳዎችና ዞኖች እንዳይዛመት ተቀናጅቶ መስራት እንደሚያስፈልግም ጠቅሰዋል።

ከዚህ ባለፈም የመፀዳጃ ቤት አጠቃቀምና የንጽህና አጠባበቅን ጨምሮ ለወረርሽኙ መስፋፋት ምክንያት የሆኑ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋልም ነው ያሉት።

ወረርሽኙ በክልሉ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ 1 ሺህ 144 ሰዎች የተጠቁ ሲሆን፥ 30 ያህል ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተገልጿል።

መረጃው የደቡብ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት ነው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.