Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ትሥሥር ኘሮጀክት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ሽግግር እና ቀጠናዊ ትሥሥር ኘሮጀክት የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

ከዓለም ባንከ በተገኘ 293 ሚሊየን ዶላር የሚተገበረው ፕሮጀክት ኢትዮጵያ፣ ኬኒያ እና ታንዛንያን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።

ኘሮጀክቱ በየሀገራቱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና ዘርፍ የሚተገበር ነው መባሉን ኢቢሲ ዘግቧል።

በኢትዮጵያ 7 የቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና ማዕከላትን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ መቀመጡ ይታወሳል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.