Fana: At a Speed of Life!

ለሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ለሚንቀሳቀሰው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ልዩ ሃይል ሽኝት ተደረገለት

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጁንታውን ቡድን በመደምሰስ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር የሚደረገውን ዘመቻ ለማገዝ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ልዩ ሃይል ሽኝት ተደረገለት፡፡
የጁንታው ቡድን በኢትዮጵያ ላይ የከፈተውን ሀገር የመበታተን ተግባር ሙሉ በሙሉ በማክሸፍ የህዝቦችን አንድነት መመለስ የልዩ ሃይሉ ዓላማ መሆኑን የክልሉን ፕሬዚዳንት በመወከል አቶ ቢኒያም መንገሻ ተናግረዋል።
በፖለቲካው መድረክ ሽንፈትን የተከናነበው ይህ ስግብግብ ጁንታ÷ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የቀበራቸው የተንኮል ፈንጅዎች ችግር የፈጠሩ ቢሆንም በሰላም ወዳዱ ህዝብና በሰራዊቱ ከፍተኛ ጥረት ሃሳቡ እንዳይሳካ ተደርጓል ብለዋል።
የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋሹ ዱጋዝ በበኩላቸው ÷ ይህ አጥፊ ቡድን ከውጭ የሀገራችን ጠላቶች ጋር በመቀናጀት የፈጸመው እኩይ ተግባር ምንጊዜም የታሪክ ተወቃሽነትን የሚያሳይ ነው ያሉት፡፡
ቡድኑን ለመደምሰስ አደራ የተሰጣቸው የልዩ ሃይል አባላት በድል አድራጊነት እንደሚመለሱ ሙሉ ተስፋ እንዳላቸው መናገራቸውን ከመተከል ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላከታል፡፡
የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስትን በመወከል የተገኙት ኮሎኔል ፋሲል ይግዛው÷ የልዩ ሃይሉ አባላት በህወሓት ጠንሳሽነት በዞኑ የተፈጠረውን የሰላም ዕጦት ወደነበረበት ሰላም ለመመለስ የከፈሉት መስዋዕትነት የጀግንነታቸው ማሳያ መሆኑን አውስተዋል፡፡
አሁንም በሰሜን ግንባር ተገኝተው ከሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ጋር በመሆን ይህን አኩሪ ተግባር መፈጸም እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.