Fana: At a Speed of Life!

የሕዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በዓባይ የውኃ መጠን ላይ ተፅዕኖ አልፈጠረም- ሱዳን

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ጋር ተያይዞ በዓባይ የውኃ መጠን ላይ ተፅዕኖ አለመፈጠሩን የሱዳኑ አል-ሩሳሬስ ግድብ ዋና ዳይሬክተር ሐሚድ ሞሐመድ ዓሊ አስታወቁ።
እንደ ሐሚድ ሞሐመድ ገለፃ ኢትዮጵያ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት ብትጀምርም በጥቁር ዓባይ የውኃ ፍሰት ላይ ልዩነት አልታየም፡፡
ዳይሬክተሩ እንዳሉት ከፈረንጆቹ ሚያዚያ ወር ጀምሮም በኢትዮጵያ አዋሳኝ ድንበር ላይ ያለው የአል-ዴይም ጣቢያ ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን በሚመጣው የውሃ መጠን ላይ ምንም ዓይነት የመቀነስ ሁኔታ አልታየበትም፡፡
ምንጭ፡-ሽንዋ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.