ዓለምአቀፋዊ ዜና

ጃኮብ ዙማ የፍርድ ሂደታቸውን በበይነ መረብ ተከታተሉ

By Tibebu Kebede

July 19, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ የፍርድ ሂደታቸውን በበይነ መረብ ተከታትለዋል፡፡

ዙማ በቀረበባቸው የሙስና ወንጀል በቁጥጥር ስር ውለው ማረሚያ ቤት መግባታቸው ይታወሳል፡፡

የፍርድ ሂደታቸውን ዳኞች እና እሳቸው በተሳተፈቡት በበይነ መረብ የተካሄደ ሲሆን፥ ዙማም የማረሚያ ቤት ገጽታ በሌለው አንድ ክፍል ውስጥ ሆነው ጉዳያቸውን መከታተላቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ዙማ የፍርድ ሂደትን በማስተጓጎል ጥፋተኛ ሆነው መገኘታቸውን ተከትሎ ከአንድ ሳምንት በላይ በማረሚያ ቤት ቆይተዋል፡፡

የእርሳቸውን እስር ተከትሎ የተፈጠረ ግርግርም ከ200 በላይ ሰዎች ህልፈት ምክንያት ሲሆን የንብረት ዘረፋ እና ውድመት አስከትሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!